አዲስ ዘመን አርብ ግንቦት 7 ቀን 2018ዓ.ም
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ኢትዮ ቴሌኮም
ደቡብ ምሥራቅ ሪጅን በሪጅኑ ሥር የተለያዩ ቦታዎች ላይ ያሉትን የማስታወቂያ ሥራዎችን በማስታወቂያ ዘርፍ የተሰማሩትን ድርጅቶችን
በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡
RFQ
No. 4283857
በዚሁ መሠረት
በማስታወቂያ የሥራ ዘርፍ የተሰማራችሁ፣ ሕጋዊ የታደሰ ፍቃድ ያላችሁና ቢያንስ አንድ ዓመት የሥራ ልምድ ያላችሁ በጨረታው ለመሳተፍ
የምትፈልጉ ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ አዳማ
ከተማ ኦሮሚያ ልማት ማኅበር ሕንጻ 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመሥሪያ ቤቱ ሶርሲንግ ክፍል በመቅረብ ስለጨረታው መረጃ ማግኘትና የማይመለስ
ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሠነድ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን።
መስፈርቶች
1. ጨረታው
ከግንቦት 10 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም 5፡00 ሰዓት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል፤
2. ተጫራቾች
በጨረታ ለመሳተፍ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ የሆኑና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች
ከዚህ በፊት በማስታወቂያ ዘርፍ የሠሩበትን የሥራ ልምድ የጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች
በጨረታው ለመሳተፍ ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ/ የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ሲ.ፒ.ኦ በኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምሥራቅ ሪጅን ስም
አሠርተው ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል።
5. ተጫራቾች
በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው መፈረም አለባቸው።
6. ተጫራቾች
የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ያለው ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡።
7. ጨረታው
ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግንቦት 25 ቀን 2018 ዓ.ም 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
ይከፈታል::
8. መሥሪያ
ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጫራቾች የጨረታ
ሰነዱንና ሲፒኦ በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
ለተጨማሪ መረጃ
በስልክ ቁጥር 022-11-0994 / 022-112-166 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምሥራቅ ሪጅን
Telecommunication
Ethio telecom, previously known as the Ethiopian Telecommunications Corporation, is an Ethiopian telecommunication company serving as the major internet and telephone service provider. Ethio telecom is owned by the Ethiopian government and maintains a monopoly over all telecommunication services in Ethiopia.