Tenders

ኢትዮ ቴሌኮም የህንጻ ማሳመር ስራ፣ የጥበቃ ቤት፣ደረቅ ሽንትቤትና የአጥር ስራ በግንባታ gc/bc 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

አዲስ ዘመን ቅዳሜ መጋቢት 26 ቀን 2018ዓ.ም

የጨረታ ማስታወቂያ

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን በአዋሽ መልካሳ፣ዴራ፣አርሲ ስሬ፣ኢተያ፣ሁሩታ፣ዲክሲስ፣ጎንዴ፣ቆቃ፣አለም ጤና፣መቂ፣አዳሚቱሉ፣ቡልቡላና በገላን የህንጻ ማሳመር ስራ፣ የጥበቃ ቤት፣ደረቅ ሽንትቤትና የአጥር ስራ በግንባታ ዘርፍ የተሰማሩና ደረጃቸው GC/BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ኮንትራክተሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ RFQNo 4283714,4283790,4283794,4283798,4283724,4283801,4283786,4283784,4283796,4283770,4283771,4283783 እና 4283800 ቅደም ተከተል ፡፡

በዚሁ መሰረት በግንባታ ዘርፍ የተሰማራችሁ፣ህጋዊ የታደሠ ፍቃድ ያላችሁና ቢያንስ ሁለት አመት የስራ ልምድ ያላቸው በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ደረጃ GC/BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆናችሁ ኮንትራክተሮች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ አዳማ ከተማ ኦሮሚያ ልማት ማህበር ህንጻ 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመስሪያ ቤቱ ሶርሲንግ ክፍል በመቅረብ ስለጨረታው መረጃ ማግኘትና የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሠነድ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

መስፈርት

1. ጨረታው ከመጋቢት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል፤

2. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የታደሠ የንግድ ፈቃድ፣የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ የሆኑና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

3. ተጫራቾች ከዚህ በፊት በግንባታ ዘርፍ የሠሩበትን የስራ ልምድ የጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ብር 25,000.00/ ሃያ አምስት ሺህ/ የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ሲ.ፒ.ኦ በኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን ስም አሠርተው ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

5. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸሳን በትክክል ጽፈው መፈረም አለባቸው፡፡

6. ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ያለው ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡

7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሚያዚያ 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡

8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱንና ሲፒኦ በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 022-111-0994/ 022-112-66ዐ ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም

ደቡብ ምስራቅ ሪጅን

ETHIO TELECOM

Telecommunication

ETHIO TELECOM

ethiotelecom.et

Ethio telecom, previously known as the Ethiopian Telecommunications Corporation, is an Ethiopian telecommunication company serving as the major internet and telephone service provider. Ethio telecom is owned by the Ethiopian government and maintains a monopoly over all telecommunication services in Ethiopia.

Code: AFRO-325558 Type: Ncb - national competitive bidding Language: Amharic Region: South ethiopia regional state Source: Addis zemen Security amount: 25,000.00 Document amount: 300.00 Published: 04-Apr-26 (4 hours ago) Deadline: 28-Apr-26 (24 days left)