የጨረታ
ማስታወቂያ ቁጥር SC/L/WRM/002/2018
ኢትዮ
ቴሌኮም ለድርጅቱ አገልግሎት የማይሰጡ አዳዲስ እና ከአገልግሎት የተመለሱ የተለያዩ የእጅ ሞባይሎች ቀፎዎች፤ የቤት ስልኮች እና ሞደሞች፣ የፓወር እና
ኔትዎርክ ስፔር ፓርቶች፣ የፊክስድ ኔትዎርክ ዕቃዎች፣ የተለያዩ ዐይነት ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተር ሲፒዩ እና ሞኒተሮች፣ የተለያዩ ዓይነት ራኮች፣ የኔትዎርክ አንቴናዎች፣ ከአገልግሎት የተመለሱ ፕሪንተሮች፣
ፋክስ ማሽኖች፤ ሲግኒቸር ፓዶች፤ ስካነሮች እና የኮምፒውተር አክሰሰሪዎች፣
ያገለገሉ ላፕቶፖች፣ ከአገልግሎት የተመለሱ የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች፣ የተለያዩ የመኪና ስፔር ፓርቶች፣ የተለያዩ
ያገለገሉ ሰርቨሮች፣ የተለያዩ የአይሲቲ ስፔር ፓርቶች፣ ከአገልግሎት የተመለሱ ስክራኘ የፖል እንጨቶች፣ ብረታብረቶችንና ራኮችን ባሉበት
ቦታና ሁኔታ በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከህዳር 12 ቀን 2018
ዓ.ም እስከ ህዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ድረስ በማንኛውም ጊዜ እና ሰዓት ከኦክሽን ኢትዮጵያ ዌብ ሳይት
ወይም ከኦክሽን ኢትዮጰያ መተግበሪያ በመግባት ማግኘት እና መመዝገብ የምትችሉ ሲሆን ንብረቶቹን መመልከት እንዲሁም ተጨማሪ መረጃ ማግኘት
የምትፈልጉ ተጫራቾች አቃቂ በሚገኘው የድርጅቱ ዋና ግምጃ ቤት ፣ በወሎ ሰፈር በሚገኘው የኩባንያው
ዕቃ ግምጃ ቤቶች እንዲሁም በምስራቅ አዲስ
አበባ (ገርጂ)፣ በሰሜን አዲስ አበባ (ፈረንሳይ) እና በምዕራብ አዲስ አበባ (አስኮ) በመገኘት የታደሰ
መታወቂያችሁን በመያዝ መጎብኘትና መመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ኘሌይ ስቶር (Auction
Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et ላይ በመመዝገብ መወዳደር ይችላሉ፡፡
የኦክሽን ኢትዮጵያ
መተግበሪያ አጠቃቀምን በተመለከተ በኦክሽን ኢትዮጵያ የጥሪ ማዕከል 9164/ 090511-5511 ወይም 0116-66-8828
ደውሎ መረዳት ይቻላል፡፡
ኩባንያው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ
የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም
Telecommunication
Ethio telecom, previously known as the Ethiopian Telecommunications Corporation, is an Ethiopian telecommunication company serving as the major internet and telephone service provider. Ethio telecom is owned by the Ethiopian government and maintains a monopoly over all telecommunication services in Ethiopia.