Tenders

ኢትዮ ቴሌኮም የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረታብረቶችን ለብረታብረት ፋብሪካዎች ቅድሚያ በመስጠት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

አዲስ ዘመን ሀሙስ ግንቦት 7 ቀን 2017 ዓ.ም

ከአገልግሎት የተመስሱ የተስያዩ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ የመጣ ገልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 07/2017

የጨረታ ሰነዱ የሚሸጥበት ቀን ግንቦት 11 ቀን 2017 ዓ.ም፣ ጨረታው የሚዘጋበት ቀን ግንቦት 28 ቀን 2017 ዓ.ም፣ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ግንቦት 29 ቀን 2017 ዓ.ም፣ ኢትዮ ቴሌኮም በሰሜን ምስራቅ ሪጅን ስር የሚገኙ ከአገልግሎት የተመለሱ የተለያዩ ቁርጥራጭ ብረታብረቶችን ባሉበት ሁኔታ ለብረታብረት ፋብሪካዎች ቅድሚያ በመስጠት በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከግንቦት 11 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ግንቦት 28 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ደሴ/ፒያሳ በሚገኘው የኢትዮ ቴሌኮም ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል እና በመግዛት መወዳደር የምትችሉ ሲሆን ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የምትፈልጉ ተጫራቾች ደሴ/መላኩ አካባቢ በሚገኘው ዋናው ዕቃ ግ/ቤት ቢሮ በመገኘት መጠየቅ ይቻላል፣ እንዲሁም ንብረቶቹን መመልከት ለሚፈልጉ ደሴ ካራጉቱ በሚገኘው ዕቃ ግምጃ ቤት የታደሰ መታወቂያችሁን እና የጨረታ ሰነዱን የገዛችሁበትን ደረሰኝ በመያዝ መጎብኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ደሴ/ፒያሳ በሚገኘው ዋናው ጽ/ቤት ግንቦት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል። ኩባንያው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የሰ/ምስ/ሪጅን ኢትዮ ቴሌኮም

ETHIO TELECOM

Telecommunication

ETHIO TELECOM

ethiotelecom.et

Ethio telecom, previously known as the Ethiopian Telecommunications Corporation, is an Ethiopian telecommunication company serving as the major internet and telephone service provider. Ethio telecom is owned by the Ethiopian government and maintains a monopoly over all telecommunication services in Ethiopia.

Code: AFRO-305789 Type: Ncb - national competitive bidding Language: Amharic Region: Amhara region Source: Addis zemen Security amount: Document amount: 300.00 Published: 15-May-25 (4 days ago) Deadline: 05-Jun-25 (17 days left)