Tenders

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን በአቦምሳና በደሎመና የሻወርና የመጸዳጃ ቤት ስራ / በግንባታ ዘርፍ የተሰማሩና ደረጃቸው gc/bc 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ኮንትራከተሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

አዲስ ዘመን እሁድ ሚያዚያ 12 ቀን 2017 ዓ.ም

በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን በአቦምሳና በደሎመና የሻወርና የመጸዳጃ ቤት ስራ / በግንባታ ዘርፍ የተሰማሩና ደረጃቸው GC/BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ኮንትራከተሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት በግንባታ ዘርፍ የተሰማራችሁ፣ ሕጋዊ የታደሰ ፍቃድ ያላችሁና ቢያንስ ሁለት አመት የስራ ልምድ ያላቸው በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ ደረጃ GC/ BC 7 እና ከዚያ በላይ የሆናችሁ ኮንትራክተሮች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ አዳማ ከተማ ኦሮሚያ ልማት ማህበር ህንጻ 5ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የመስሪያ ቤቱ ሶርሲንግ ክፍል በመቅረብ ስለጨረታው መረጃ ማግኘትና የማይመለስ ብር

200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታውን ሠነድ በመግዛት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

መስፈርት፡-

1. ጨረታው ከሚያዝያ 16 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ድረስ ከፍት ሆኖ ይቆያል፤

2. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ የታደሠ የንግድ ፈቃድ፣የተእታ ተመዝጋቢ የሆኑና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል::

3. ተጫራቾች ከዚህ በፊት በግንባታ ዘርፍ የሠሩበትን የስራ ልምድ የጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል::

4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ብር 20,000.00/ ሀያ ሺ) የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ሲ.ፒ.ኦ

በኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን ስም አሠርተው ከጨረታ ሠነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል::

5. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው መፈረም አለባቸው።

6. ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ ሲሞሉ ስርዝ ድልዝ ያለው ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡

7. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሚያዝያ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡

8. መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱንና ሲፒኦ በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ በተዘገጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 022-11-0994 / 022-112-1660 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ምስራቅ ሪጅን

ETHIO TELECOM

Telecommunication

ETHIO TELECOM

ethiotelecom.et

Ethio telecom, previously known as the Ethiopian Telecommunications Corporation, is an Ethiopian telecommunication company serving as the major internet and telephone service provider. Ethio telecom is owned by the Ethiopian government and maintains a monopoly over all telecommunication services in Ethiopia.

Code: AFRO-304605 Type: Ncb - national competitive bidding Language: Amharic Region: South western ethiopia peoples regional state Source: Addis zemen Security amount: Document amount: 200.00 Published: 20-Apr-25 (5 days ago) Deadline: 07-May-25 (11 days left)