Tenders

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ሪጅን ጽ/ቤት ለኮንክሪት መንገድ ሥራ፣ የአጥር እና ጥበቃ ቤት እና የግንብ ሥራን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

አዲስ ዘመን ሐሙስ ጥር 29 ቀን 2017 ዓ.ም

የውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ፣ አጥር እና ጥበቃ ቤት ሥራ የጨረታ ማስታወቂያ

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ሪጅን ጽ/ቤት ከታች በሰንጠረዥ በተገለፀው ፓኬጅ መሰረት ለኮንክሪት መንገድ ሥራ፣ የአጥር እና ጥበቃ ቤት እና የግንብ ሥራን ከታች በተገለጸው ደረጃ የሆኑ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በዘርፉ የሥራ ፈቃድ ያላችሁ እና ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ ድርጅቶች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን ከሐዋሳ ዋናው ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 103 በመቅረብ የማይመለስ 200 ብር ከፍለው ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

በተጨማሪም በኦንላይን www.merkato.com, www.afroteneder.com and www.extratender.com መግዛት ይችላሉ፡፡

ደረጃ

የሥራው አይነት

የሥራው ቦታ

ፓኬጅ

የጨረታው መለያ ቁጥር

ጨረታው የሚጀምርበት ቀን

ጨረታው የሚቆይበት ጊዜ

የጨረታው መዝጊያ ቀን እና ሰዓት

የጨረታው መክፈቻ ቀን እና ሰዓት

የጨረታው ማስከበሪያ መጠን በብር

5 እና ከዚያ በላይ

ኮንክሪት መንገድ ሥራ

ሀዋሳ ሪጅን ጽ/ቤት

1

4272027

የካቲት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት

15 ቀን

የካቲት 19 ቀን 2017 ዓ.ም በ11፡00 ሰዓት

የካቲት 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት

10,000.00

5 እና ከዚያ በላይ

የግንብ ሥራ

ፊንጩ ውሃ

2

4272028

የካቲት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት

15 ቀን

የካቲት 19 ቀን 2017 ዓ.ም በ11፡00 ሰዓት

የካቲት 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት

10,000.00

5 እና ከዚያ በላይ

አጥር እና ጥበቃ ቤት

ሻሸመኔ

3

4272026

የካቲት 4 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት

15 ቀን

የካቲት 19 ቀን 2017 ዓ.ም በ11፡00 ሰዓት

የካቲት 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት

20,000.00

መስፈርቶች፡-

1. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ የሚችል፤

2. የ2017 ዓ.ም ግብር የከፈለ እና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፤

3. የቫት እና የቲን ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፤

4. ለአጥር እና ጥበቃ ቤት በደረጃ አምስት (5) እና ከዛ በላይ ሆኖ አንድ የስራ ልምድ ያለው በዘርፉ አንድ የመልካም ሥራ አፈፃፀም፤ የክፍያ ሰርተፊኬት እና ውል ማቅረብ የሚችል፤

5. በገቢዎች አስተዳደር ባለሥልጣን በጨረታ ላይ መሳተፍ የሚያስችል ደብዳቤ ያለው እና ደብዳቤውን ማቅረብ የሚችል፤

6. ተጫራቾች ፋይናንሻል ዋናውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ፣ ቴክኒካል ዶክመንት ዋናውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ፣ ፋይናንሻል ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ (ሁለት ኮፒ)፣ ቴክኒካል ዶክመንት ኮፒውን (ሁለት ኮፒ) በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ እንዲሁም ሲፒኦ ለየብቻ በአንድ እናት ፖስታ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ሪጅን ጽ/ቤት

ETHIO TELECOM

Telecommunication

ETHIO TELECOM

ethiotelecom.et

Ethio telecom, previously known as the Ethiopian Telecommunications Corporation, is an Ethiopian telecommunication company serving as the major internet and telephone service provider. Ethio telecom is owned by the Ethiopian government and maintains a monopoly over all telecommunication services in Ethiopia.

Code: AFRO-299862 Type: Ncb - national competitive bidding Language: Amharic Region: Addis ababa city administration Source: Addis zemen Security amount: Document amount: 200.00 Published: 06-Feb-25 (1 month ago) Deadline: 25-Feb-25 (-17 days left)