አዲስ ዘመን ሀሙስ ታህሳስ 24 ቀን 2017ዓ.ም
ያገለገሉ የተለያየ ሞዴል ያላቸው ላፕቶፖች
ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ኢትዮ ቴሌኮም ያገለገሉ ላፕቶፖችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
1 ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ተጫራቾች ከታህሳስ 30 እስከ ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከአፍሮቴንደር
(www.afrotender.com) ወይም ከቱመርካቶ (www.2Merkato.com) ድረገጾች ላይ መግባት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ
ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በቴሌ ብር በመከፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
2. እቃዎች ለማየት ተጫራቾች ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ አቃቂ በሚገኘው የኢትዮ ቴሌኮም ዕቃ
ግምጃ ቤት በመገኘት ከታህሳስ 30 ቀን እስከ ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ - አርብ ማየት ይችላሉ።
3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚመለስ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የመግዣ
ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በቴሌ ብር ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
4. የጨረታው ሰነድ ገቢ የሚደረገው አቃቂ በሚገኘው የኢትዮቴሌኮም ዕቃ ግምጃ ቤት ሲሆን ተጫራቾች ወይም
ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥር 16 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት አቃቂ በሚገኘው ኢትዮቴሌኮም ዕቃ ግምጃ ቤት ይከፈታል፡፡
5. ዝርዝር መረጃውን ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም
Telecommunication
Ethio telecom, previously known as the Ethiopian Telecommunications Corporation, is an Ethiopian telecommunication company serving as the major internet and telephone service provider. Ethio telecom is owned by the Ethiopian government and maintains a monopoly over all telecommunication services in Ethiopia.