Tenders

ኢትዮ ቴሌኮም ያገለገሉ የተለያየ ሞዴል ያላቸው ተሽከርካሪዎችና ጄኔሬተሮችን እንዲሁም አዳዲስ እና ከአገልግሎት የተመለሱ የተለያዩ የኔትዎርከና የፖወር ዕቃዎች፣ ያገለገሉ ባትሪዎች፣ያገለገሉ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችና ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን ባሉበት ሁኔታ ለብረታ ብረት አቅላጭ ፋብሪካዎች ብቻ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

አዲስ ዘመን ማክሰኞ ታህሳስ 22 ቀን 2017 ዓ.ም

የጨረታ ማስታወቂያ ያገለገለ ተሽከርካሪዎች፣ ጄኔሬተሮች እና ስክራፕ እቃዎች ሽያጭ

ኢትዮ ቴሌኮም ያገለገሉ የተለያየ ሞዴል ያላቸው ተሽከርካሪዎችና ጄኔሬተሮችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

እንዲሁም አዳዲስ እና ከአገልግሎት የተመለሱ የተለያዩ የኔትዎርከና የፖወር ዕቃዎች፣ ያገለገሉ ባትሪዎች፣ያገለገሉ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችና ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን ባሉበት ሁኔታ ለብረታ ብረት አቅላጭ ፋብሪካዎች ብቻ በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

1. ዝርዝር መረጃ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ተጫራቾች ከታኅሣሥ 25 ቀን 2017ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከአፍሮ ቴንደር(. afrotender.com) ወይም ከቱመርካቶ (www.2 merkato.com) ድረ-ገጾች ላይ በመግባት ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በቴሌ ብር በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

2. እቃዎቹን ለማየት ተጫራቾች ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ በመያዝ አቃቂ በሚገኘው የኢትዮ ቴሌኮም ዕቃ ግምጃ ቤት በመገኘት ከታኅሣሥ 25 ቀን ጀምሮ እስከ ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ - አርብ ማየት የሚችሉ ሲሆን ነገር ግን በጨረታ መዝጊያው ቀን ጥር 15 እስከ ጠዋት 6፡30 ድረስ ብቻ ማየት የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚመለስ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የመግዣ ዋጋውን 10% (አስር በመቶ) በቴሌ ብር ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

4. የጨረታው ሰነድ ገቢ የሚደረገው አቃቂ በሚገኘው የኢትዮ ቴሌኮም ዕቃ ግምጃ ቤት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥር 16 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት አቃቂ በሚገኘው ኢትዮ ቴሌኮም ዕቃ ግምጃ ቤት ይከፈታል፡፡

5. ዝርዝር መረጃውን ከጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም

ETHIO TELECOM

Telecommunication

ETHIO TELECOM

ethiotelecom.et

Ethio telecom, previously known as the Ethiopian Telecommunications Corporation, is an Ethiopian telecommunication company serving as the major internet and telephone service provider. Ethio telecom is owned by the Ethiopian government and maintains a monopoly over all telecommunication services in Ethiopia.

Code: AFRO-297488 Type: Ncb - national competitive bidding Language: Amharic Region: Addis ababa city administration Source: Addis zemen Security amount: Document amount: 500.00 Published: 31-Dec-24 (2 weeks ago) Deadline: 22-Jan-25 (5 days left)